ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመርን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ የ11 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ የ11 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ጨምሮ፥ በሌሎች አራት የቀድሞ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

የፌደራል መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው በመርማሪ ፖሊስ የተጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውስጥ 11 ቀን የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ እና ሌሎች የቀድሞ የክልሉ ባለስልጣናት ባለፈው አመት በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸው አለበት በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።(ኤፍ ቢ ሲ)