ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቱርክ አቅንተዋል

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት  ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በትላንትናው እለት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቱርክ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ወደ ቱርክ ያመሩት በቱርክ አፍሪካ የቢዝነስ መድረክ ላይ እንዲገኙ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ፡፡

መድረኩ የቱርክ ባለሀብቶች በአፍሪካ ውስጥ ያላቸውን ኢንቨስትመንት እንዲያሰፉና እንዲያጠናክሩ የጎላ ሚና  ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከቱርክ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከትላልቅ የኩባንያ ኃላፊዎች ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ፡፡

በመድረኩ ላይ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፓል ካጋሜ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀማት እንደሚገኙም ይጠበቃል፡፡ (ምንጭ፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት)