ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አስመራ ገቡ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አስመራ ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ማምሻውን አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረዓብ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ትናንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

በቆይታቸውም ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በአርባ ምንጭ እና በጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ የሚገኘውን የሰቃ ፏፏቴን ጎብኝተዋል።

በወቅቱም የኢፌዴሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተገኝተዋል።

የጅማ ባህላዊ የቡና አፈላል ስነ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን፥ የዞኑን የተለያዩ ቅርሶች የሚያሳይ ስጦታም ተበርክቶላቸዋል።(ኤፍ ቢ ሲ)