ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ከስሎቪኒያው አቻቸው ጋር ውይይት አደረጉ

ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የስሎቪኒያው ፕሬዝዳንት ቦሩት ፓሆር ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ፣ አህጉር አቀፍና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በንብ ማነብ፣ በቱሪዝም፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ረገድ በጋራ የመስራት እቅድ አንዳላቸው መክረዋል፡፡

አንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1991 ከቀድሞ ዩጎዝላቪያ ራሷን ነጥላ ያወጣቸው ስሎቪኒያ በከፍተኛ መሪ ደረጃ ፕሬዝዳንት ፓሆር ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ኢትዮጵያን ባለምቀፍ መድረክ በዲፕሎማሲ፤ በኢንቨስትመንት፤በከባቢ ብክለት ብሎም በሰወች ፍልሰት ተመሳሳይ አቋም ያለቸው በመሆኑ ተመራጭ አድርገው ወደዚህ ማቅናታቸው ታውቋል፡፤

በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ እያደገ በመጣው ምጣኔ ሀብታዊ እድገቷና የውጪ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ተመራጭ መሆኗን ያነሱት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ቁልፍ ከሆኑ ነጥቦች መካከል በንብ ማነብ፣ በቱሪዝም፣ ንግድ እና ኢንቨስትንት ዘርፎች በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን አንስተዋል፡፡

የስሎቪኒያው ፕሬዝዳንት በበኩላቸው አትዮጵያና ስሎቪኒያ በባህል ተመሳሳይነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ያነሱ ሲሆን ሀገራቸው በቀጣይንት ከአፍሪካ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደ ድልድይ መጠቀም እንደሚፈልጉና ያላቸውንም የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር አንደሚፈልጉ አንስተዋል፡፡

ውይይቱን የተከታተሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በጣልያን በኩል ስሎቪኒያ ደግሞ በብራዝልስ በኩል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን እንደሚያከናውኑ ገልጸው በቀጣይ በሁለቱ ሀገራት ኤምባሲ ለመክፈት ጥናት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ስሎቪኒያ ከአውሮፓ ህብርት አባል ሀገራት አንዷ ስትሆን ከአትዮጵያ ጋር በመሆን አለማቀፋዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት ያለቸው ሀገራት ናቸው፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመም በቀጣይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ስሎቪኒያ እንደሚያቀኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡