የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲና አራት ተቋማት ተጠሪነታቸው ለምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲን ጨምሮ አራት ተቋማት ተጠሪነታቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲሁም የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነታቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን ወስኗል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የአካባቢ፣ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያና የቤተ መንግስት አስተዳደር ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ተወስኗል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የመንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የሚወስነውን አዋጅ ቁጥር 1097/2011 በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።