የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሰ ጫፎን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ በማድረግ ሾሟል ።
አቶ ታገሰ ጫፎ ከዚህ ቀደም ከዞን አንስቶ በክልልና በፌዴራል ደረጃ በተለያዩ የአመራርነት እርከኖች አገልግለዋል፡፡
የምክር ቤቱ ብቸኛ እጩ የነበሩት አቶ ታገሰ በሙሉ ድምጽ በመመረጣቸው በምክር ቤቱ ደንብ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሆነዋል፡፡
የምክር ቤቱ አፈጉባዔ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን በመተካት ነው አቶ ታገሰ እንዲሾሙ ያደረገው ።