ምክር ቤቶቹ ነገ የፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማሉ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማሉ ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓ.ም ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት።

ሶስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ነገ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ስልጣን ያስረክባሉ። (ምንጭ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት)