አዲሱ የጋህአዴን አመራር ራሱን ከጎሰኝነትና ጥላቻ በማጽዳት ችግሮችን ሊፈታ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሳሰቡ

አዲሱ የጋህአዴን አመራር ራሱን ከጎሰኝነትና ጥላቻ በማጽዳት የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳስበዋል፡፡

የጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስትን በመምራት ላይ ሚገኘው የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ የማዕከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የጀመረው ግምገማ እንደቀጠለ ነው፡፡

በግምገማው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የክልሉ ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር ጊዜውን በግል አጀንዳዎችና ሽኩቻ ከማጥፋት ይልቅ ራሱን ከጎሰኝነትና ከጥላቻ በማጽዳት የክልሉን አመራር በማጠናከር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ በርካታ ሙያተኞች በየዩኒቨርሲቲው፣ በፌዴራል፣ በክልሉም ሆነ በዳያስፖራ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን በማፈላለግ በየደረጃው ክልሉን ለማጠናከር ቅድሚያ ሠጥቶ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡        

በእስካሁኑ ግመገማው የፓርቲው ሊቀመንበር እና የክልሉ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑነት አቶ ጋትሉዋክ ቱት እና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር ከኃላፊነታቸው ለቀዋል፡፡   

ፓርቲው በምትካቸው አቶ ኦሙድ ኡጁሉን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አኙአያ ጃከን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ታውቋል፡፡

ከኃላፊነት የተነሱት አመራሮችም በድርጊታቸው ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸው እና ህዝቡን ለመካስ በተመደቡበት የስራ መስክ ለመሰማራት መወሰናቸው መልካም መሆኑ ተጠቁሟል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው አስታውቋል፡፡