የአማራ ክልል ምክር ቤት 3ኛ ዙር 4ኛ ዓመት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 3ኛ ዙር 4ኛ ዓመት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤቱ የ3ኛ ዙር 4ዓመት ጉባኤ የመወያያ አጀንዳዎች ለጉባኤተኛው በመቅረብ ላይ ናቸው።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው የክልሉ ብዙሀን መገናኛ ድርጅትን የ2010 በጀት ዓመትና የ2011 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ይገመግማል።

ከዚህ ባለፈም የ2011 በጀት ዓመት የትምህርት አጀማመርና የክልሉን ትምህርት ቢሮ የ2011 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሞ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በጉባዔው የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅን፣ የአስፈጻሚ አካላትን እንደገና ማቋቋሚያ፣ ስልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያፀድቅም ነው የሚጠበቀው።

የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና ስፖርት ኮሚሽን እንደገና እንደሚቋቋሙም ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።