የደቡብ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ የቢሮ ሀላፊዎችንና ሌሎች ሹመቶችን አፀደቀ

ለቀናት ጉባኤውን በሃዋሳ ሲያካሂድ የቆየው የደቡብ ክልል ምክር ቤት በተሻሻለው የክልሉ መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ መሰረት አዳዲስ የቢሮ ኃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

  1. አቶ ወንድሙ ገብሬ፦ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
  2. አቶ ታምራት ዲላ፦ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
  3. አቶ ኑሪዬ ሱሌ፦ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኃላፊ
  4. አቶ ጥላሁን ከበደ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ
  5. ዶ/ር ጌትነት በጋሻው፦የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
  6. አቶ አብርሀም ማርሻሎ ፦ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
  7. አቶ ክፍሌ ገ/ማሪያም ፦ በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
  8. አቶ አንተነህ በፍቃዱ ፦የውሀ ማእድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
  9. ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ፦ በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
  10. አቶ አቅናው ካውዛ ፦ የጤና ቢሮ ኃላፊ
  11.  አቶ አክሊሉ ለማ ፦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ
  12. ወ/ሮ አስቴር ከፍታው ፦የሴቶች ፥ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
  13. አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ፦ የኢንተርፕራይዞችና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
  14. አቶ ንጉሴ አስረስ ፦ የገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ
  15. ወ/ሮ ሰብለ ፀጋ ፦ የባህል ፥ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
  16. አቶ ኤልያስ ሽኩር ፦ ም/ር/መስተዳደርና የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
  17. አቶ ሀልገዮ ጂሎ ፦ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
  18. ዶ/ር ሃሚድ ጀማል ፦ የእንስሳት እና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱን በአፈ ጉባኤነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ መልቀቂያን በመቀበል በምትካቸው ወይዘሮ ሄለን ደበበን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል። (ምንጭ የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ)