ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና የካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ትናንት እለት በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ውይይት አድርገዋል ።
የካናደው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎም በአሁኑ ወቅት በሴቶችን በቁልፍ የመንግስት አመራር ቦታዎች መሳተፍ መንግስታቸው ማድነቁን ገልጸዋል ።
የካናዳ መንግሥት ይህንን በሙሉ ልብ ለመደገፍና ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን ገልፀውላቸዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የመጣውን ለውጥ በኋላም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ መድረክ እየተጫወተች ያለውን ሚና ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል ።
በስልክ ውይይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በቅርቡ ኢትዮጵያን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ለጠቅላይ ሚንስት ዶክተር አብይ ገልጸዋል ።(ምንጭ: የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)