በብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ ብሔሮች የአንድ ሌላ ብሔር ባህላዊ የአለባበስና ጭፈራ ትርዒት ያሳያሉ

በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረው የዘንድሮ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ ብሔሮች ከራሳቸው በተጨማሪ የአንድ ሌላ ብሔር ባህላዊ የአለባበስና ጭፈራ ትርዒት እንደሚያሳዩ ተጠቆመ። 

የ13ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ዝግጅት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ -ጉባዔ፣ የክልሎች ምክር ቤቶች አፈ -ጉባዔዎች የበዓሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት  በአዲስ አበባ ተገምግሟል። 

በዓሉ ሃገራዊ አንድነት፣ ሰላምና መቀራረብ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ነው ተብሏል።

ከእነዚህም መካከል የራስ ብቻ ሳይሆን አንዱ ብሔር የሌላውንም ባህል ጨምሮ እንዲያሳይ ለማድረግ ሁሉም የቤት ሥራ ወስዶ ዝግጅት እንዲጀምር ተደርጓል።

በሃገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ደግሞ ግጭቶች ተከስተው በነበሩባቸው አካባቢዎች ላይ ሁሉም የሚሳተፍበት ህዝባዊ መድረክ በማዘጋጀት ውይይትና እርቅ እየተደረገ መሆኑንም ተመልክቷል ።(ኢዜአ)