20ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚዎች አስቸኳይ ስብሰባ ተጀመረ

20ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚዎች አስቸኳይ ስብሰባ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተጀምሯል፡፡

የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ተወካዮች በተገኙበት የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋቂ መሀማት ስብሰባውን በንግግር ከፍተዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በንግግራቸው የህብረቱ አስቸኳይ ስብሰባ በተለያዩ አህጉራዊ የጋራ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፉት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የስራአስፈፃሚዎቹ አስቸኳይ ስብሰባዉ በመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎችን ማርቀቅ፣ በህብረቱ ተቋማዊ ሪፖርት በማቅረብ፣  የህብረቱ ቀቋሚ ኮሚቴዎች የሚያስተላልፉት ውሳኔ ላይ መምከር፣ የህብረቱ የልማት ኤጄንሲ(AUDA) እና የህብረቱ የፋይናንስ ድጋፍ ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡