ሁሉም ፓርቲዎች የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የበኩላቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል- ፓርቲዎች

ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመጣውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ  እንደሚገባ  ሦስት ተፎካካሪ  ፓርቲዎች  ገለጹ ።

የአፋር ህዝቦች ፓርቲ፣ የአዲስ ትውልድ ፓርቲና አንድነት ፓርቲ አመራሮች ለዋልታ እንደገለጹት  መንግሥት የጀመረውን  የለውጥ እንቅስቃሴ  አጠናክሮ  ለማስቀጠል  ሁሉም  ተፎካካሪ  ፓርቲዎች  የበኩላቸውን  አስተዋጽኦ ማበርከት  ይገባቸዋል ብለዋል ።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያሏቸውን የልዩነት ሓሳቦች ወደጎን  በመተው  አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ  የበኩላቸውን  ኃላፊነት  እንዲወጡም  የፓርቲ አመራሮቹ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

የአፋር ሕዝቦች ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ሙሳ አደም እንደገለጹት ለህዝብ አገልግሎት እየሠጡ ያሉት  በለውጡ አስተሳሰብ  የተቃኙ ለማድረግ  አስፈላጊውን ትምህርትና ሥልጠና መሥጠት  እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።

የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ትዕግስቱ አወሉ በበኩላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት  የደረሰባቸው  ዜጎችን  መንግስት እራሱን የቻለ ተቋም በመመሥረት በኢኮኖሚም ሆነ በስነ ስነ ልቦና ረገድ  ድጋፍ  ሊያደርግላቸው ገባል ብለዋል ።

ሌላው የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ( አትፓ) አመራር የሆኑት አቶ ሰለሞን ደነቀ  እንደገለጹት የተፎካካሪ ፓርቲዎችና አባሎቻቸው ሙስና በማጋለጥ ረገድ መንግሥት የጀመረውን እንቅስቃሴ በተግባር  እንዲያግዙ  ጥሪ አቅርበዋል ።