ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከካናዳው የልማት ሚንስትር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከካናዳው መንግስት ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ማሪ ክሎድ ቢቦን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ዛሬ የካናዳ መንግስት ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ማሪ ክሎድ ቢቦንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ቢቦም የካናዳ መንግስት ኢትዮጵያ እየተጓዘች ያለችበትን የዴሞክራሲንና የልማት ለውጥ ጉዞ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት ጥረቶች የካናዳ መንግስት ስለመደገፉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል ።

ቢቦ በበከሉላቸው እንዳርጋገጡት በቅርብ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ጉብኝት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።( የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት)