ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአፋር ክልል ከፍተኛ ኃላፊዎችና የአብዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአፋር ብሄራዊ ክለላዊ መንግስት አመራሮችና የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተወያዩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተደረገው ውይይት ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀናጀት በክልሉ ደረጃ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈንና ለማጠናከር እንዲሁም ጎን ለጎን ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ መስማማታቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረዉን ለዉጥ በክልሉ ደረጃ በመተግበር ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድርግ ስምምነት ላይ መደረሱንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም እየተፈጸመ ያለዉን ሃገራዊ ለዉጥ ህዝባዊ መሠረትን ይዞ የክልሉን ወጣቶችንም ባሳተፈ መንገድ ተፈጻሚ እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡(ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)