በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ የዕርቅና የሠላም ኮንፈረንስ ተካሄደ

በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ የዕርቅና የሰላም ኮንፈረንስ በሓዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ ትናንት ተካሄደ።

በእርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሲዳማና ወላይታ ዞን የተወጣጡ የኃይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከሁለቱም ዞኖች የተወጣጡ የባህል ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ነዉ
የዕርቅና የሠላም ኮንፈረንሱ የተካሄደዉ።

በኮንፈረንሱ የተገኙት የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የኢፌደሪ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሀት ካሚል፥ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል በተፈጠረው የዕርቅና የሠላም ኮንፈረንስ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

ይህን ዕርቅ እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ አክብሮታቸውንና አድናቆታቸዉን አቅርበዋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)