የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ከንቲባው ወደ ባህርዳር ሊያቀኑ ነው

300 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ  ወጣቶችና ምክትል ከንቲባው  ወደ  ባህር ዳር ሊያቀኑ ነው ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) እና 300 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የፊታችን አርብ (ህዳር 14/2011ዓ.ም) የአማራ ክልል ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ውቢቷ ባህር ዳር ያመራሉ፡፡

በከንቲባው የሚመራው የልዑካን ቡድን በሶስት ቀን የባህርዳር ቆይታው ብሄራዊ ሃብታችን የሆነውን ጣናን እየተፈታተነ ያለውን የእንቦጭ አረምን ያርማል፥ የህዝብ ለህዝብ ውይይት ከከተማዋ ወጣቶች እና ከከተማዋ ኃላፊዎች ጋር ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሰል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች በቀጣይነትም ከኦሮሚያ ፥ ከትግራይ እና ሌሎችም የሃገሪቱ ክፍሎች ጋር ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል። (ምንጭ: የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ቢሮ)