ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ አዲስ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው አዲስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ  ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን እንደሚሾም ይጠበቃል። 

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ሰብሳቢን በእጩነት ለመምረጥ የቀረበ የውሳኔ ሓሳብን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ መሾማቸው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ምከር ቤቱ በነገው ስብሰባ ያልተሟሉ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበሮችን  ሹመት ለማፅደቅ የሚቀርብለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅም መረጃች ያመለክታሉ፡፡