የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሓመድናሌሎች የክልሉ ባለሥልጣናት ከ2004 እስከ 2010 ድረስ በሶማሌ ክልል አስተዳደር ላይ ተቃውሞ ያሰሙ 200 የክልሉ ተወላጆች እንዲገደሉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ፖሊስ በምርመራ ሥራው ማወቁን ገልጿል ።
አቶ አብዲና ሌሎች የሶማሌ ክልል አመራሮች በሥልጣን በነበሩበት ወቅት በተፈጸመው ኢ -ሰብዓዊ ድርጊት 200 ያህል ሰዎች ለስድስት ዓመታት ውስጥ መገደላቸውን መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ጠዋት በተካሄደው ችሎት ላይ አስረድቷል ።
ፖሊስ ጉዳዩን ይበልጥ ለማጣራትና የሟቾችን ማንነት ለመለየት የተቀበሩባቸውን ሥፍራዎች በውል ለማየትም ፍርድቤቱን የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ገደብ እንዲሠጠው ጠይቋል ።
የእነ አብዲ ኤሌ ጠበቆች በበኩላቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ የተፈጸሙ ወንጀሎች በዚህ ክስ ላይ መካተት እንደሌለበትና ለመርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ እንደሌለበት ተከራክረዋል ።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ፖሊስ የክስ መዝገብን በመመልከት መርማሪ ፖሊስ ሥራውን በተገቢ መልኩ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
በተጨማሪም በመርማሪ ፖሊስ የቀረበውና የሴማሌ ክልል አመራሮች ፈጽመውታል የተባለውን የኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በዚህ መዝገብ መካተት የለበትም የሚለውን ችሎቱ ውድቅ አድርጓል ።
በእነ አብዲ ኤሌና ሌሎች የሶማሌ ክልል አመራሮች የተከፈተው ክስን የፌደራል ፖሊስ መርማሪ እንዲያጣ የተጠቀውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮን ፍርድ ቤቱ በመፍቀድ ቀጣይ ችሎቱ ህዳር 27 እንዲካሄድ ወስኗል ።