በደቡበ ሱዳን ወቅታዊና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው 2ኛው የኢጋድ ኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ ተካሄደ

በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ፣የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረው 2ኛው የኢጋድ አባል አገራትና ሩዋንዳ የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ  በመኮንኖች ክበብ ተካሂዷል ።

ከወር በፊት የተካሄደው የመጀመሪያው የኢጋድ አባል አገራት የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ  ሩዋንዳ  በተሳተፈችበት  የደቡብ  ሱዳንን  ወቅታዊ ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳይን የሚከታተል የቴክኒካል  ኮሚቴን ማቋቋሙ ይታወሳል ።

አዲስ  አበባ  እየተካሄደው  ባለው ስብሰባው ላይ የኢፌዴሪ  መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ  መሐመድ ንግግር ያደረጉ ሲሆን  የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚ ኃይሎች ሰላምና ፀጥታን  ለማረጋገጥ  የሚያደርጉትን ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል ።

እንደ ኢንጂነር አይሻ ገለጻ የደቡብ  ሱዳን ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥም  ሁሉም  የህብረተሰብ ክፍል  የድርሻውን  መወጣት  እንዳለበት  ተናግረዋል ።

የኢጋድ የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ  በዛሬ  አጀንዳውም  የተቋቋመው የቴክኖካል ኮሚቴ   እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራትም ላይ ውይይት  እየተደረገ ሲሆን  የደቡብ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ  የሚያስችሉ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል ።