አዲሱ የፓለቲካ ባህላችን ሰጥቶ መቀበልን እንድንለምድ ግድ ይለናል- ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ

“በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ተግዳሮቶች፣ እድሎችና መሰናክሎች” በሚል ርዕስ ሀገር አቀፍ መድረግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይግኛል።

በዚህ መድረክ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የሀብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደትምተገኝ በንግግራቸው አንስተዋል።

ጥያቄው ግን ይህንን ለውጥ እንደ ወርቃማ እድል ተጠቅመን እንጓዛለን ወይስ በለውጡ የተመዘገቡ ውጤቶችን እንቀለብሳለን የሚለው ነው ብለዋል።

በመቀጠልም አሁን የምንገኝበት ዘመን የተለያዩ የፖለቲካ ሀሳቦችን የምናንሸራሽርበት እንደሆነና፥ አዲሱ የፓለቲካ ባህላችንም ሰጥቶ መቀበልን እንድንለምድ ግድ ይለናልም ነው ያሉት።