በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ሠራዊቱ የሚደግፈው መሆኑን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ ።
በሚኒስቴሩ የኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሠጥተዋል ።
ሜጀር ጄነራል በመግለጫቸው እንደገለጹት በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ አካላትም ካሉ መከላከያ ህገመንግሥቱን መሠረት በማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል ።
መከላከያን ከሜቴክ ጋር በማገናኘት በሠራዊቱ ላይ እየተካሄደ ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻን እንደሚያወግዙት ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተናግረዋል ።