በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዘጠኝ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ።

ሰልፎቹ በደቡባዊ፣ ማዕከላዊና ምዕራባዊ ዞኖች በሚገኙ ዘጠኝ ከተሞች ማለትም በአድዋ፣ አክሱም፣ ኮረም፣ አዲ ሽሁ፣ አላማጣ፣ መኾኒ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ዓብይ ዓዲ እና ራያ አዘቦ ከተሞች ላይ ነው ተካሂዷል። 

በሰልፎች ላይ “ፍትህ በሁሉም አካባቢ ይንገስ፣ የህግ የበላይነት ይከበር፣ ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት እንጂ በሌሎች አካላት መዳኘት የለባቸውም፣ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ለሰላም እንተባበር” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን አሠምተዋል።

በተለይም በምዕራባዊና ደቡባዊ ትግራይ ዞኖች በተካሄዱት ሰልፎች ላይ “በማንነት ጥያቄ ስም የሚቀርብ ጥያቄ እኛን አይወክልም” የሚል መፈክርን ይዘው ወጥተዋል።

በተጨማሪም ሰልፉ ላይ የተገኙ የከተሞቹ ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡ (ኤፍቢሲ)