የትግራይ ክልል ለ3 ሺህ 231 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ3 ሺህ 231 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

የትግራይ ክልል የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንደገለጸው፥ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 72 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ።

ክልሉ የይቅርታ ህግንና መሥፈርት በመመሥረት ነው ታራሚዎቹ በይቅርታ እንዲለቀቁ የተደረጉ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ ተኪኡ ምትኩ ተናግረዋል።

ታራሚዎቹ ከህዳር 20 ቀን 2011 ጀምሮም  መደበኛ  ህይወታቸውን ለመጀመር ወደ ህብረተሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተመልክቷል።

የክልል መንግስት ባለፈው ዓመት የግንቦት 20 በዓልን ምክንያት ለ2 ሺህ 206 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።