የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጊ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ  አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ሪቦር ናጊ በጉብኝታቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ በጅቡቲ፣ ኤርትራና ኬንያን  ይጎበኛሉ ተብሎ  ይጠበቃል ።

ቲቦር ናጊ በዛሬ ዕለት በጀመሩት በጉብኝታቸውም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት  ጋር በኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ።

ረዳት ሚንስትሩ በአፍሪካ  ቀንደ  አገራት  ጉብኝታቸው ከአፍሪካና በአሜሪካ  የንግድ ፣ በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በጋራ በምትሠራባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚመክሩም ነው የተገለጸው።

የአፍሪካ ህብረት በአዲስ አበባ በሚያካሂደው ከፍተኛ የምክክር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናጊ በጉብኝታቸውም በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በጅቡቲ ተገናኝተው እንደሚመክሩ ከወዲሁ የወጣው ፕሮግራም  ጠቁሟል፡፡

ረዳት ሚኒስትሩ የንግድ ኃላፊዎችን እንዲሁም የአፍሪካ ወጣት መሪ ተወካዮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ገልጿል ።