የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው የከፍታችን ዋና ምሰሶው ፍቅር ሲሆን፥ ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በመተሳሰብ እና በመፈቃቀድ ከፍታቸውን ጠብቀው በጋራ የሚኖሩባትና በምሳሌነትም የምትጠቀስ ከተማ ነች ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ይህን አረዓያነት የማስቀጠል ኃላፊነት እንደለባቸውም አሳስበዋል።

ወጣቱ ትውልድ ተራራ ለመውጣት ብሎም አስፈለጊ ሆኖ ሲገኝ መናድ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ከፍታውን ሲጠብቅ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አልፎ አልፎ ከዚህ ከፍታችን የሚያወርዱ ትርክቶች ተከትሎ የሚፈጠሩ ችግሮች ለችግር የሚዳርጉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ደግሞ አብሮነት፣ በፍቅር መተሳሰብና መፈቃቀድ መሆኑን አመልክተዋል።

አባቶቻችን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር በማስከበር የተዋደቁት የኢትዮጵያን ከፍታ ለዚህ ትውልድ ለማስተላለፍ ነውም ብለዋል።