በሀገር ውስጥ የነበሩ ሁለት ፓርቲዎችና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ አምስት ፓርቲዎች ውህደት ፈጠሩ

በሀገር ውስጥ የነበሩ ሁለት ፓርቲዎችና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ አምስት ፓርቲዎች አንድ ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን የውህደት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ፓርቲዎቹን ወክለው ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት አመራሮች አንድ ትልቅ ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን ባለፉት ስድስት ወራት ስጠናኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ውህደት የፈጠሩት ፓርቲዎቹም የኢትዮጵያ መድህን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ራዕይ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ሽግግር) ብሩህ ኢትዮጵያ ዴሚክራሲያዊ ንቅናቄ (ብሩህ)፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዴሚክራሲያዊ ድርጅት (ቱሳ)፣ አንድ ሀገር አንድ ህዝብ ኢትዮጵያችን ህዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) እና የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኦሞ ህዝቦች) መሆናቸውም ተገልጸዋል፡፡

ሁሉም የራሳቸው ርዕዮተ ዓለም ቢኖራቸውም አገራዊ መግባባት መፈጠር መቻላቸውና ተበታትነው ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል አንድ ሆነው የተጠናከረ ተፎካካሪ ፓርቲ ለመሆን መዋሄዳቸውም ተነግሯል፡፡

ፓርቲዎቹ የራሳቸውን አስተሳሰባቸውን ስያራምዱ ቢኖሩም አንድ ኢትዮጵያ በሚለው ዓላማ ስለተግባቡ ለመዋሄድ መወሰናቸውን ገልጸዋል፡፡