የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሆነ ተገለጸ

የኦስትሪያው መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ የፊታችን ሀሙስ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተገለጸ። 

መራሄ መንግስት ሰባስቲያን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚቻሉበት ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በጀርመን በርሊን በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ መገነኘታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በተገናኙበት ወቅትም የሁለትዮሽ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን ሀገራቱ የጋራ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር በትብብር እንደሚሰሩ ተስማምተዋል፡፡