ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሴባስቲያን ከርዝ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መከሩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሴባስቲያን ከርዝ  ጋር   በመገናኘት  በሁለቱ አገራት  ግንኙነትና  በተለያዩ ዓለም አቀፍ  ግንኙነት  ዙሪያ ምክክር  አድርገዋል ።

የኦስትሪያው መራሂ  መንግሥት  ሴባስቲያን  ከርዝ የጠቅላይ  ሚንስትር  ጽህፈት ቤት  ሲደርሱ  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  የክብር  አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

ሰባስቲያን ከርዝ ጠዋት  ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሱበት ወቅትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በተሳተፉበትና በጀርመን በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተገናኝተው ውይይት  ማድረጋቸው  ይታወሳል

ሁለቱ  መሪዎች  በጀርመን  ባደረጉት ውይይት ወቅትም  የጋራ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር በትብብር እንደሚሰሩ መስማማታቸው ይታወሳል።