ፍርድ ቤቱ በያሬድ ዘሪሁን፣ በተስፋዬ ኡርጌና ሜጀር ጀነራል ክንፈ ላይ የተጠየቀውን የ14 ቀን ምርመራ ፈቀደ

ፍርድቤቱ በያሬድ ዘሪሁን፣ በተስፋዬ ኡርጌና ሜጀር ጄነራል ክንፈ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ ።

በትናንትናው ዕለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ፣ ተስፋዬ ኡርጌና ሜጀር ጀነራል ክንፈ እንዲቀርቡ ተደርጓል ።

ፍርድ ቤቱ በያሬድ ዘሪሁን ላይ ከህዳር 26 2011 ጀምሮ ታሳቢ የሚሆን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።    

በበተስፋዬ ኡርጌ  መዝገብ  ላይ ፍርድ ቤቱ ከህዳር 24 2011 ጀምሮ ታሳቢ የሚሆን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ከተጠርጣሪዎች ጋር ተያያዥ የሆኑ  ማስረጃዎች  በፖሊስ  እየተሰበሰበ ሲሆን የሚቀረው ሥራ በመኖሩ በዋስ ቢወጡ ማስረጃ እንደሚያጠፉ ስለታመነበት ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል ተብሏል። 

የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤት ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለታህሳስ 10 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘውን ጉዳይ  የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ለቀሪ  የምርመራና  የሥራ ማጠናቀቂያ ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን የፈቀደ  ሲሆን  ከህዳር 24 ጀምሮ የሚቆጠር በመሆኑ ፥ ለታህሳስ 4 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ጠበቆች ትናንት በዋለው ችሎት በመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ላይ ሓሳብ እንደሚያቀረቡ የገለጹ ቢሆንም ሳያቀርቡ ቀርተዋል።

ፍርድ ቤቱ ከሜቴክ ሠራተኞች ጋር ተመሳጥረው ከሁለት የውጭ ድርጅቶች የድለላ ፍቃድ ሳይኖራቸው ከተገዛ 2 ሺህ 500 ትራክተር 15 ሚሊየን ብር ለግል ጥቅማቸው በማዋል በተጠረጠሩት አቶ ረመዳን ሙሳ ላይ ለታህሳስ 10 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሙስና በተጠረጠሩት እነ የጋዜጠኛ ፍጹም የሽጥላ ፣ ትግስት ታደሰ እና ቸርነት ዳና ላይ ፖሊስ ቀደም ብሎ በተሰጠው ምርመራ ጊዜ የሰራውን በርካታ ስራ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።