13ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው

13ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው።

ዘንድሮ በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት የሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነት በዓል እያንዳንዱ ብሔር የየራሱን ባህልና ወግ የሚያጎላበት ብቻ ሳይሆን አንዱ የሌላውን በማጌጥ ከልዩነት ይልቅ በአንድነት መተሳሰር የሚጎላብት ሁነት ነው።

በዓሉ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የብሔሮች ተወካዮች፣ ተማሪዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት የማጠቃለያውን ፕሮግራም ይካሄዳል።

በተያዘው መርሃ ግብርም የመከላከያና ፖሊስ ማርሽ ባንዶች፣ የማስ ስፖርት ትርኢቶች፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች የባህል ትርኢቶች ደምቀው የሚታዩበት ይሆናሉ።

በተጨማሪም  የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የመዲናዋ ምክትል ከንቲባ፣ የምክር ቤቶች አፈጉባዔዎችና የጎረቤት አገራት መሪዎች መልዕክቶች እንዲሁም የሄሊኮፕተር  እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት  እና የሽልማት ስነ ስርዓቶች  በበዓሉ ላይ በሚከናወኑ ሁነቶች ወስጥ እንደሚገኙ ተገልጸዋል።

ሰሞኑ ከተማዋ በልዩ ልዩ ፓናል ውይይቶች፣ አውደ ርዕይዮች፣ የሙዚቃ ድግሶች፣ ሲምፖዚየሞች፣ ባዛሮች፣ የጎዳና ላይ ትርኢቶችና ለሰላም ቡና ጠጡ ፕሮግራሞች ደምቃ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡