ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጅማ ከተማ ገቡ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጅማ ከተማ ገብተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች ጅማ ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የሚመራው የመንግስት አመራሮች ልኡክ ጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የከተማዋ የስራ ሀላፊዎችና የአካባቢው ህዝብ አቀባበል አደርገውላቸዋል።

በጅማ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርና የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ይቀበላሉ።

በተጨማሪም በከተማዋ የተገበኑ የተለያዩ የልማት ፕሮጀትኮችን የሚመርቁ ሲሆን፥ ከሀገራቱ መሪዎች ጋር በመሆንም የከተማዋን የልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ።