የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የጂቡቲ መሪዎች የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ማዕከልን መረቁ

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከል በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከልን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርና የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው በይፋ መርቀው የከፈቱት።

የሜዲካል ማዕከሉ 800 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ማዕከሉ እንደ ደቡብ ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራትም አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተገነባ መሆኑም ተነግሯል።

ዩኒቨርሲቲው ያስገነባው ይህ የሜዲካል ማዕከል በጤናው ዘርፍ የምርምር፣ የማስተማሪያ፣ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

በተያያዘ ዩኒቨርሲቲው 131 የህክምና እጩ ምሩቃን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2 ሺህ የድህረ ምርቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን ያስመርቃል።