ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ በባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ወይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጊኒር ወረዳ አርዶ ቀብሶ ቀበሌ ከብሪታኒያው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌየር ጋር በመሆን በአካባቢው በክላስተር የለማ የስንዴ እርሻን ጎብኝተዋል።

በስንዴ  ማሳ ጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ ተገኝተዋል ።

በቀበሌው አርሶ አደሮች በ2 ሺህ 350 ሄክታር መሬት ላይ በ133 ክላስተሮች የዱረም ስንዴን በማምረት ላይ ይገኛሉ።