ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ሥራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ጋስፓርድ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ፓትሪክ ጋስፓርድ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የለውጥ ሂደት ላይ ማተኮሩን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ሥራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ጋስፓርድ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው ልማት ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል፡፡

ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ግንባታ አላማዎችን በተለይም የፍትህ ስርዓት ማሻሻያና ተቋማትን በማጠናከር ዙሪያ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳለውም ስራአስኪያጁ በውይይታቸው ተናግረዋል፡፡