የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ አወንታዊ የለውጥ እርምጃዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ አቋም እንዳለው በአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ እርዳታና የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ኪርስቶስ ስታይሊ አንዲስ ገለጹ፡፡ 

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኮሚሽነሩን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በኮሚሽነሩ በዚህ  ወቅት እንደገለጹት፥  መንግስት እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ከአካባቢው አልፎ ለአፍሪካ ጭምር ጠቃሚ ልምዶችን የሚሰጥ ነው፡፡

ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር በተለያየ መንገድ የምታደርጋቸውን ትብብሮች ማጠናከር እንደምትፈልግ ተናግረዋል።(ምንጭ: የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት)