አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የክልሉ ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በተዘጋጀ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አጽድቆታል።

ምክር ቤቱ በቀጣይም አፈ ጉባኤውን በመምረጥ በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የካቢኔ አባላትን ሹመት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። ኤፍ.ቢ.ሲ