በህገ-ወጥ መንገድ ታጥረው የቆዩና ወደ መንግስት መሬት ባንክ ገቢ የተደረጉ ቦታዎች ለህዝብ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህገ-ወጥ መንገድ ታጥረው የቆዩ እና ወደ መንግስት መሬት ባንክ ገቢ የተደረጉ መሬቶች ለህዝብ አገልግሎት መሥጠት መጀመሩን የከንቲባው ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለትም የከተማ አስተዳደሩ ህንፃ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ በከፊል ጊዜያዊ የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አገልግሎት ማዋሉ ተገልጿል፡፡

የጊዜያዊ ፓርኪንጉ መጀመርም በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀርፍ ሲሆን ቦታም በቋሚነት ለህዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንደሚውል የከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ መግለፁ ይታወቃል፡፡ (ምንጭ፡-የከንቲባ ጽህፈት ቤት)