ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አዳዲስ ሹመቶች መስጠታቸው ተገለጸ

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዩ የፌደራል ተቋማት አዳዲስ ሹመቶች መሥጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1 አቶ ኃይላይ ብርሀኔ ተሰማ- የጠቅላይ ሚንስትሩ ብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ፣

2 ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ- የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣

3 አቶ ሳንዶካን ደበበ- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣

4 ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ዋና ዳይሬክተር፣

5  አቶ ተመስገን ጥላሁን- የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ም/ዋና ዳይሬክተር፣

6  አቶ ሙሉቀን ቀረ- የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር፣

7 አቶ ገብረመስቀን ጫላ- የኢትዮጵያ ካይዘን አንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር    ሆነው መሾማቸው ተገልጿል ።