ኳታር ለስምንት ኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት አደረገች

ኳታር ለስምንት ኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት ማድረጓ ተገልጿል።

የኳታሩ አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ የሀገሪቱን ብሄራዊ በዓል ቀን ምክንያት በማድረ ግ ለስምንት የህግ ታራሚዎች ምህረት ማድረጋቸው ተነግሯል።

በቀጣይም በእስር ላይ የሚገኙ 18 ኢትዮጵያውያንን ለማስፈታት በኳታር የኢፌዴሪ ኤምባሲ ክትትል እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በምህረት የተፈቱት ኢትዮጵያውያንም በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለጸው።(ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)