ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሪፑብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት ጋር ተገናኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሪፑብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት ጋር ተገናኝተዋል፡፡

የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይል አባላትም የመንግስት ባለስልጣኖች እና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከልና ለማዳን ዝግጁነታቸውን የሚያሳይ ትርዒት አቅርበዋል፡፡

የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይሉ የአገሪቱን ሕገ-መንግሥትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመ የደህንነት መስሪያ ቤት አካል ነው፡፡

ይህ የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል በከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ያሉትን ኃላፊዎች ከማንኛውም ስጋት እና ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዘዴ መጠቀም ዋነኛ ተግባሩ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ባለፉት 6 ወራትም ይህ ኃይል እራሱን በሰለጠኑ የደህንነት ባለሙያዎችና በተገቢው መንገድ ተግባሩን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን እያደራጀና ስልጠናዎች እያደረገ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ያቀረቡት ትርዒትም ማናቸውንም ጥቃቶችን ለማስቆምና ለመመከት ያለውን ዝግጁነትና ሙሉ አቅሙን ለማሳየት የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)