በኦሮሚያ የህዝብንና የመንግስት ሀብት በማባከን የተጠረጠሩ 56 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ክልል የህዝብንና የመንግስት ኃብት በማባከን የተጠረጠሩ 56 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የህዝብና የመንግስትን ሀብት ያለአግባብ ያባከኑ 56 የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ሲያደርግ የነበረውን ጥናት አጠናቆ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ነው የገለጸው፡፡

ተጠርጣሪዎችን ለሕግ የማቅረብ ስራ ተጠናከሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ በሙስና ላይ እየተደረገ ያለው ትግልና በአሁኑ ወቅት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን አስመልክቶ የኮሚሽኑ አመራሮች በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጡ በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል፡፡ (ምንጭ፡-ኦቢኤን)