“የእንግሊዝና የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል”–ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

የእንግሊዝና የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የልማት ድጋፍ በማጠናከር የሀገሪቱን የእድገት ጉዞ መደገፏን እንደምትቀጥል ተሰናባቿ የእንግሊዝ አምባሳደር ተናግረዋል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሱዛን ሙርሄድ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የለውጥ ሂደት ሀገራቸው ድጋፍ እንደምትሰጥ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው እንግሊዝ የምታደርገው የልማት እገዛ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

እንግሊዝ በየዓመቱ 300 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደርስ የልማት ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምታደርግ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡(ምንጭ፡-የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት)