በሀገሪቱ ተስፋ ሰጪ ለውጥ እየታየ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ አንድነት መድረክ ገለጸ

በሀገሪቱ ተስፋ ሰጪ ለውጥ እየታየ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ አንድነት መድረክ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ አንድነት መድረክ ትላንት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተጀመረው ሃገራዊ ለውጥ የህብረተሰቡን ጥያቄ በመመለስ ረገድ የሚቀሩት ነገሮች ቢኖሩም ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጋብዞ ተቀራርበን እንወያይ የሚል መንግስት መኖሩም የለውጥ ሂደቱ የተሻለ መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

በጉባኤው ቀጣይነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማስፈን መድረክ የበኩሉን አስተዋጽኦ አንደሚያደረግም አስታውቋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)