ኢትዮጵያ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የነበራትን የሁለት ዓመት ቆይታ አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የነበራትን የሁለት ዓመት ቆይታ በተሳካ ሁኔታ ትላንት ታህሳስ 22፤2011 ዓ.ም በይፋ አጠናቃለች፡፡

አትዮጵያ በነበራት የሁለት ዓመታት ቆይታ የተባበሩት መንግስታት መርሆዎች በትክክል እንዲከበሩና ተግባራዊ እንዲዲደረጉ አበክራ መስራቷ ነው የተገለጸው፡፡

ከሁሉም አባል አገራት ጋር በትብብር መንፈስ በመስራት የአገሯን ብሄራዊ ጥቅምም አስከብራለች ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በዓለም ላይ የሚታዩ አለመግባባቶች በሰላምና በድርድር እንዲፈቱ የሚጠበቅባትን አዎንታዊ ሚና በአግባቡ መወጣቷንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)