በባህርዳር ከተማ በአንድ ኮማንደር መኖሪያ ቤት 498 ህገ-ወጥ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በባህርዳር በአንድ ኮማንደር መኖሪያ ቤት 498 ህገ-ወጥ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡

በዛሬው ዕለት ነው በኮማንደሩ መኖሪያ ቤት በክልሉ ፖሊስ ህገ ወጥ መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ  ኤኮል ፒ 29  የተባሉ ቱርክ ሰራሽ 180 ሽጉጦች  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን  ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር  ስር ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

ከዚህ በላፈ በተለያዩ ወቅቶች በህብረተሰቡ ተሳትፎና በፀጥታ አካላት በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ወደ ሀገር ወስጥ ሲገቡና ሲንቀሳቀሱ  እንደተያዙ ይታወቃል፡፡

(ምንጭ ፡ ኤፍ.ቢ.ሲ)