ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአፍሪካን ቀልብ መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው -ሲኤን ኤን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የመላው አፍሪካን ቀልብ መሳብ መቻላቸውን የአሜሪካው  ሲኤንኤን ዘገባውን አቀርቧል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከገባችበት የብሔር ግጭትና ውጥረት እንድትወጣና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር በአሁኑ ወቅት እየሠሩ መሆናቸውን  ጠቁሟል ።

በኢትዮጵያ የታሠሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ ብሎም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን   ሁሉ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረው የረጅም ጊዜ ውጥረት ወጥተው ወደ ሰላም እንዲገቡ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የሚታየውን ግጭት ለማስወገድ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲን ያካተተ የጋራ ውይይት በማድረግ የተጫወቱት ሚናም ከፍተኛ እንደነበር ተጠቅሷል ፡፡

የአፍሪካ አገራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአፍሪካ ተስፋ ሰጪ የሆነ ተግባር ያከናወኑና  ፣ዴሞክራሲን ተግባራዊ ለማድረግ እየሠሩ የሚገኙና ኢትዮጵያን ከገባችበት ችግር ያወጡ መሆናቸው  ያምኑባቸዋል፡፡(ምንጭ: ሲኤን ኤን)