አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ በመሆን ተሾሙ

አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡

አቶ ንጉሱ ጥላሁን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፎ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡

ለረጅም ዓመታትም የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል፡፡

አቶ ንጉሱ ከዚህ ቀደም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሆነው  የተሾሙት  ቢልለኔ ስዩምን ተክተው  እንዲሠሩ ነው የተሾሙት  ፡፡

በተያያዘም አቶ ካሳሁን ጎፌ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ምክትል በመሆን ተሾመዋል።

አቶ ካሳሁን ከዚህ ቀደም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን እና በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው አገልግለዋል። 

(ምንጭ:አመብድ)