የቀድሞ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሲሳይ ነጋሽን ጨምሮ 5 ግለሰቦች በሙስና ተጠርጥረው ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

የቀድሞ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሲሳይ ነጋሽን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ጠርጥረው በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የኦሮሚያ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አቶ ሲሳይ ነጋሽ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብና የመንግስትን ንብረት መዝብረዋል ተብለው መጠርጠራቸው ነው የተገለጸው፡፡

አቶ ሲሳይ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የመንግስት እርከኖች በአመራርነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የአሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት 75 ተጠርጣሪዎችን በሙስና በመጠርጠር በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፡-የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)